Bashewam General Secondary School - Weekly News Highlights

Thursday, February 19, 2026 By Bashewam School News


Introduction

Bashewam General Secondary School aspires to become an exemplary center of excellence by 2029 by providing an effective education system that produces nationally competitive, creative, and problem-solving citizens. Our mission is centered on quality education, community ownership, and the development of ethical citizens.



1. Road Safety Awareness Campaign

On February 9, 2018 E.C., the school's Road Safety Club broadcasted a special program via mini-media to enhance student safety and reduce traffic accidents. Coordinated by teachers Kuri Kebede and Siranesh Alem, the broadcast included a road safety song and a detailed explanation of traffic light signals. Teacher Kuri emphasized that when traveling, students must maintain full focus on the road and moving vehicles to stay safe.

2. Gender Club Awareness Program

On February 11, 2018 E.C., the Gender Club presented a broadcast to promote equality and mutual respect among students. Led by teachers Etsubdink and Tigist, the program featured:

  • Inspirational Message: Student Sina delivered a powerful message on the importance of gender equality and encouraging female students to excel in their studies.

  • Eva Show: An engaging interview segment discussing current topics related to gender and school life.

  • Music: Student Abigiya performed "Yegar Kasma" (Pillar of the Nation), a song celebrating the strength of women and their role in nation-building.



Core Values & Closing

We remain committed to our values of transparency, integrity, and collaboration. By solving educational problems through research and study, we continue to prepare our students for a changing world. As our motto states: "Equality for better results!"

"Our safety has a big impact on our education!"


ባሸዋም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - የሳምንቱ የዜና መፅሄት

መግቢያ

በሸዋም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጤታማ የትምህርት ስርዓት በማስፈን በ2022 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ፣ በትምህርት የታነጹ እና ችግር ፈቺ ዜጎችን በማፍራት የልህቀት ማዕከል ለመሆን በራዕይ እየሰራ ይገኛል። ትምህርት ቤታችን ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ በመስጠት፣ መልካም አርአያነትን በማስፈን እና በጋራ በመስራት የሚታወቅ ተቋም ነው።



1. የመንገድ ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ

የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ቤታችን የሚገኘው የመንገድ ደህንነት ክበብ የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ያለመ ልዩ ፕሮግራም በሚኒ ሚዲያ አስተላልፏል። በመምህር ኩሪ ከበደ እና በመምህርት ስራነሽ አለም መሪነት የቀረበው ይህ ዝግጅት፣ የመንገድ ደህንነት መዝሙርን እና የትራፊክ መብራት ትርጓሜን አካቶ ቀርቧል። መምህር ኩሪ ተማሪዎች መንገድ ላይ ሲጓዙ ትኩረታቸው ሙሉ በሙሉ በመንገዱና በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

2. የስርዓተ-ፆታ ክበብ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም

የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ የስርዓተ-ፆታ ክበብ የተማሪዎችን የእኩልነት ግንዛቤ ለማሳደግና ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ተከባብረው እንዲማሩ ለማበረታታት ያለመ ፕሮግራም በሚኒ ሚዲያ አቅርቧል። በመምህር እፁብድንቅ እና በመምህርት ትዕግስት የተመራው ይህ ፕሮግራም የሚከተሉትን ይዘቶች አካቷል፦

  • አነቃቂ መልዕክት፦ ተማሪ ሲና ስለ ፆታ እኩልነት አስፈላጊነትና ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረታታ መልዕክት አስተላልፋለች።

  • ኢቫንስ ሾ (Eva Show)፦ ስለ ስርዓተ-ፆታ ዙሪያ የሚያጠነጥን ወቅታዊና ሳቢ ቃለ-መጠይቅ ቀርቧል።

  • ሙዚቃ፦ ተማሪ አቢጊያ "የሀገር ካስማ" በሚል ርዕስ በሴቶች ብርታትና የሀገር ግንባታ ሚና ላይ ያተኮረ ሙዚቃ አቅርባለች።

ማጠቃለያ

ትምህርት ቤታችን በጥናትና ምርምር የትምህርት ችግሮችን ለመፍታት እና ለለውጥ ሁልጊዜ ዝግጁ ነው። "እኩልነት ለተሻለ ውጤት!" የሚለውን መሪ ቃል በመከተል ለተሻለ ስኬት በጋራ እንሰራለን።